ሚያዝያ 17 ቀን 2010 ዓ.ም ====================
ሚያዝያ 17 ቀን 2010 ዓ.ም
====================
ሦስተኛ ቀኑን የያዘው የአማራ ክልል ምክር ቤት በዛሬው ዕለት የቅማንት ብሔረሰብ አስተዳደር ማቋቋሚያ አዋጅ ለማሻሻል የቀረበውን አዋጅ መርምሮ አንድ ተቃውሞ በሶስት ድምፀ ተኦቅቦ አፅድቋል።
በዚህም መሰረት በማንነቱ ላይ መወሰን ያለበት ራሱ የማንነት ጥያቄ ያነሳው ህዝብ በመሆኑ ቀደም ሲል ህዝቡ በምርጫ ድምፁን ሰጥቶ በወሰነው እና በህገ መንግስታችን በተደነገገው መሰረት የቅማንት ህዝብ በኩታ ገጠምነት የሚኖርባቸውን 69 ቀበሌዎች መሰረት አድርጎ ይደራጃል።
በወቅቱ ተጨማሪ ውይይት ይጠይቁ የነበሩ እና ምርጫ ያልተደረገባቸው አራት ቀበሌዎች ምርጫ ሳይደረግ በህዝቡ ምክክር ህዝቡ ወደ ፈለገበት አስተዳደር እንዲካለል ተወስኖ ይህም ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ተጠናቋል።
በክልላችን ከአሁን ቀደም በብሔረሰብ አስተዳደር ደረጃ እንደተዋቀሩት የአዊ፣ የዋግ ኸምራ እና የኦሮሞ ብሔረስብ አስተዳደሮች በወረዳዎች ይደራጃል።
የብሔረሰብ አስተዳደሩ ርዕሰ ከተማም በአስተዳደሩ ምክር ቤት ይወሰናል።
የብሔረሰብ አስተዳደሩን የማደራጀት፣ የአስተዳደሩን ርዕሰ ከተማ እና ሌሎች ጉዳዮችን የክልሉ መንግስት ከህዝቡ ጋር በመመካከር እና በመወያየት ይፈፅመዋል።

Comments
Post a Comment
Thank you for your comments.
Please make sure that you subscribed to my websites.